በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚያኖር የለም፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና፥ መቀደዱም የባሰ ይሆናል

0
1370

“በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚያኖር የለም፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና፥ መቀደዱም የባሰ ይሆናል። በአረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ አቁማዳው ይፈነዳል፥ የወይን ጠጁም ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል፤ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል፥ ሁለቱም ይጠባበቃሉ።” ማቴዎስ 9:16

በአሮጌ ጨርቅ ላይ ማንም አዲስ እራፊን አያኖርም! ለምን ከፊተኛው ይልቅ የኃላው መቦጨቅ ይብሳልና ነው:: ባረጀም አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ ይግባ ቢሉ ለመፈንዳት ነው:: አይጠባበቁም! የበበሰበሰው የወያኔ ፀረ-አማራ መንግስት ለሚደርሰው የአማራ እንግልት ገንዘብ በማዋጣት አንቀርፈውም:: አንድ ህዝብ ለልማት አዋጥቶ አገር አትገነባም::እንዲህ ያለ ጉድ ተሰምቶም ታይቶም አይታወቅም! የልጆች ጨዋታ እየሆነ ነው ጉዳያችን! አንድ ህዝብ በስደት ላይ ሆኖ በስደት ሰርቶ ካገኘው ላይ መንግስት ሆን ብሎ የሚያፈናቅለውን አገር ቤት ያለን ህዝብ መልሶ አቋቁሞ አይዘልቅም:: መፈናቀሉ ቀጣይ ነው:: መንግስት ወንበር ላይ የተቀመጠው አማራን ለማፈናቀልና ለማጥፋት ስልት አውጥቶ የመጣው የትግሬው ቡድን ወደ መንግስትነት የመጣበት አላማ ዋናው አማራን ማጥፋት ማዳከም ነውና! አንድ ህዝብ የማህበራዊ መገልገያ ተቋማታን እንዲሰሩ ግብር የሚከፍለው መንግስት ሳይሰራለት ሌላ ለህልውናው የሚታገልን የዝሁኑ የህዝብ ክፍል መሰረታዊ ልማትን አቋቁም ብሎ ማለት ድብቅ አጀንዳ እንዳለ ይነግረናል:: አእምሮ ያለው በአመክንዮ የሚያስብ ማንም ይህንን አያጣውም!

አማራው ለህልውናው በተሰባሰበ ማግስት የፈረሰ ትምህርት ቤት ስራ ብሎ ማለት ወደ ነፃነት መንገድ ከሚወስደው መንገድ ለማስወጣት የተሸረበ ደባ ነው:: መሰረታዊ ነገሮች እንዳይሰሩ ያደረገውን ፀረ-አማራ መንግስት ማውረድና የራሳችንን መንግስ ማቆም ነው እንጂ መላው በዚህ ወያኔ እያፈርሰ በዚህ ዳያስፕራው በገንዘብ ይደግፍ ማለት ደንበኛ የጠላት ተንኮል አለበት:: በማወቅም ይሁን በእልኸኝነት ይህንን ተግባር የሚፈፅሙ አካላት በጥሞና ነገሮችን ቢመረምሩ መልካም ነው::

“ከአባቱ የማይበልጥ ትውልድ እንዳልተወለደ ይቆጠራል”…. አፈወርቅ ገ/የስ
“ከክብሩ ተነጥሎ የተወለደ ልጅ እንዳልተወለደ ይቆጠራል”…… እኛ፡፡

ዛሬ ከመተከል ለተባረሩ ገንዘብ ስጡ ይባላል:: ነገ ደግሞ ከሌላ አገሪቱ ክፍል ሆን ብሎ ወያኔም ያፈናቅላል የኛ ትግል በዚህ “ጎ ፈንድ ሚ ” ገንዘብ ለቀማ ላይ ተንጠልጥሎ እንዲቀር ሲል:: ወደ ዋናው ነገር እንዳንገባ ማዘናጊያ ነው ይሄ! በዚህ ጉዳይ የተጠመዳችሁ ወገኖች ሌላው ልታጤኑት የሚገባው ሴራ (አላስተዋላችሁ እደሆን) ወያኔ አገር ቤት ያለውን አማራ ከርስት እያባረረ ርስት አልባ ሲያደርግ ባንድ ጠጠር ሁለት ወፍ ስትመታ በውጭ ያለነውን ደግሞ በኢኮኖሚ ማዳከም ስልት ይዛ ተፈናቃዮችን እንርዳ የሚል በሰርጎ ገብ ብአዴኖቿ ታስተገብራለች ማለት ነው:: ሁላችን የምናውቀው ነው ስንት ገንዘብ ተሰብስቦ አየር ላይ ባክኖ እንደሚቀር:: እኛ በውጭ ያለን ደግሞ ህዝባችንን ከመውደድ እና ከመሳሳት ብሎም ከህሊና ወቀሳ በ$50 $100 መዋጮ ለመገላገል የምንወረውረው ፍራንክ መፍትሄ እንደማያመጣና ይልቁንም ከዋናው ትግል አደናቃፊና ጎታች ነው:: አዳካሚም ነው:: እንደ አንድ ህዝብ ክፍል ፈር የያዘ ትግል መስመር ማበጀት ሲገባ በተደጋጋሚ የተለያየ የቆዩና በወያኔ ስርአት ውስጥ እስካለን የማይለወጡ ነገሮችን እንደ አዲስ አጀንዳ እያመጡ ፖለቲካችን ፈር እንዳይለብስና እንዳይጎለብት የተለያየ አጀንዳ በማምጣት መሰናክል መሆን እናቁም::

ሌላው አማራው በደረሰበት ከፍተኛ ዘርፈ ብዙ ጉዳት በፎቶ እያስደገፉ መለመኛ ማድረግ እጅግ አስነዋሪ ተግባር ነው:: የስነልቦና ክስረት ነው:: እኔ ብሆን እዛ ቦታ መንገድ ላይ የተደፋሁት ማንም በምስሌ የለመነበት ብሎም የፌሱክ እንዲዞር የምፈልግ ይመስላችኃልን? ማንህስ ብትሆን ያንተ ጉስቁልና ቢለመንበት ደስ ይልሀልን?? ብዙዎች ወገኖቻችን እንዲህ በፎቶዋቸው እንደምንቀልድበት ቢያቁ ሞታቸውን ይመርጣሉ ጥርጥር የለኝም! ምክኒያቱም እኔ ስለነሱ ሞት ሞት ብሎኛልና:: የህዝባችንን ገመና አውጥተን ላይክ ስንለቅምበት መዋል ምኑ ይሆን የሚሰጠን እርካታ? ለምን የራሳችንን በውጭ ያለን ስደተኞች ፎቶ የአማራን ውድቀት አናሳይበትም? እኛም እኮ በአለም የተበተነው ደልቶን ሳይሆን የዚሁ የፀረ አማራው እንቅስቃሴ ውጤት ነን …..እና ለምን የራሳችንን ፎቶ የአማራ በወያኔ የደረሰበት ውድቀት ለስደት የዳረጋቸው እያልን ፎቶዋችንን አንለቅም? እኛ የተሻልን ነን ማለት ነው ከአገር ቤቱ አማራ? የሰው አገር መጥተን አስጠጉን ብለን በአገራቸው በረዳ ለምነን ወረቀት ስላገኘን አገሩን አለቅም ብሎ አገሩ ላይ የሚንገላታን አማራ የምንነግድበት በምን ሂሳብ ነው? ከዚህ በኃላ የሁላችሁንም ፎቶ እየለቀምኩኝ እኔም በገፄ የአማራ ወጣት አልዋጋ ብሎ በወያኔ ካገር ተባሮ የደረሰበት ውድቀት እያልኩ ልለጥፍ እገደዳለሁ የአገር ቤቱ አማራ ያለ ውዴታው በፎቶ የሚቸረቸርበት ከሆነ::

ተውት እንጂ ይህንን ህዝብ! ተውት በፎቶው ከንፈር አታስመጥጡበት ከንፈር መጠጣን አለመነንምና! ተውት ይህንን ህዝብ በጠላቱም ፅቅ አታስብሉበት! ገመናውን እያወጣችሁ ጀግና አትባሉበት:: ባይሆን ትንሽ dignity የሚባል ነገር አለና ወድቆም ቢሆን አለም ፎቶውን እያየ ሳይስቅበትና የችግር ማሳያ ሳይሆን በክብሩ በችግርም ቢሆን ይሙት! ተውት! ማንህም የራስህን ቤተሰብ እንዲህ ሆኖ ቢታይ አትወድም እና ስለምን በራስህ ቢደረግ የማትወደውን በሌላ ታደርጋለህ??

በውጭ ያለህ አማራ በመጠን ኑር:: ገንዘብህን ያዝ የሚመጣው በአገራችን አይታወቅምና:: ኢትዮጵያ bankruptcy ውስጥ ነች:: ዛሬ እነ አብይ አህመድ ጅቡቲ ላይ የሚደራደሩበት ገንዘብ ስለሌላቸው መብራት ሀይልንና ኢትዮቴሌኮምን አስጨምድደው ወደብ እየለመኑ ነው:: አላሙዲንም ዘርፎ የጨረሰውን የወርቅ ማእድን የሰው ጤና የሚያቃውስ ሜርኪሪ ምን ሊሰራ ተጠቀመ? ወርቅ ማንጠር ምን ሜርኪዮሪ አስፈለገው? እህች hoax ነገር ወያኔ ሲያምታታ ነው:: ጀዋርን ሲያገዋልሉ ጉዳዮ ግን ሌላ ነው…..በጭምደዳው ድርድር ከጅቡቲው ፕሬዚደንት ጀርባ የጅቡቲ ባለቤት ፈረንሳይ እንደቆመም አንዘንጋ:: እና የሀገራችን ችግር እየተወሳሰበ እነቻይና ህንድ በሚቀራመቷት ሰአት በውጭ ያለንን አማሮች የመጨረሻ resort ነንና ሊመጣ ላለው እንዘጋጅ:: በረባ ባረባ ገንዘባችንን አንበትን:: ብዙ ቀንበር አለብንና ገና::

መንግስት ለመጣል ዘይድ እንጂ በገንዘብ ማሰባሰብ ትግል የለም! በዚህ አትጠመድ! ወያኔ እስካለ ችግር አይቆምም:: እኛ ዳያፕራ ስደተኞች ደግሞ አገር ማቋቋም አንችልም:: ግብር እየተከፈለ አገሩ ላይ ገንዘብ ንዋዩን እያፈሰሰ የሚሰራው ህዝብ መንግስት ሆን ብሎ ካፈናቀለውና ልማቱን ካስተጓጎለ መፍትሄው መንግስትን ጎትቶ ማውረድ ነው!

አማራ ግብር መክፈል አቁም አሁኑኑ!ድ

ሊዲያ ዘ-ጊዮን አማራ