መደራጀት ማለት ምን ማለት ነው 101

0
1482

አማራ ሆይ መደራጀት ማለት ምን ማለት ነው? ምን ስንሆን ነው ተደራጀን የሚባለው? እነኝህ ጥያቄዎችን ስንመልስ የመደራጀት ትርጉሙ ይፈታልንና በቀላል ተግባራዊ ይሆናል:: መደራጀት ሂደት ነው:: ስልት ያለው ሂደት! መደራጀት እንዳያችሁት ላለፈው አራት አመት እንደምናደርገው ሁሉ መጀመሪያ ዋናው የማንቃት ስራ/ዘመቻ ነው እያደረግን ያለነው:: ህዝብ ሲነቃ ደግሞ ሰብሰብ ይላል ሊያወጋ:: በሩን ጥርም አድርጎ ዘግቶ ይመክራል:: ከዛም ጎበዝ አለቃውን ይሾማል:: ከዛ ከጎጃም፣ ጎንደር፣ ሸዋ፣ቤተ አማራ (ወሎ) ምስጥራዊ ድር ያደራል:: ዋሻ ዋሻውን በአራቱም ክፍላተ አገራት ጠግጥጎ ይይዛል:: በዱር ይማራል፣ ይመክራል:: በከተማ ያለውም በየስፍራው ሁለት ሶስት እየሆነ ይመክራል:: ማህበራዊ ድህረ ገፆችንም ይጠቀማል:: ከውስጥ እስከ ውጭ፣ ከዱር እስከ ዳያፕራው ድር ይምጋል:: ይያያዛል:: ሚዲያ ተጠቅሞ ሰፊ ማንቃት ስራውን ሌት ተቀን ሳይል ይቀጥላል:: በማንቃት ስራ ላይ አንድ አላማ ያስይዛል:: ታሰረ ተፈታ፣ ተያዘ ተገደለ፣ ልማቱ ቀጨጨ ገለመሌው ውስጥ ሳይገባ ስለሌላው ለማውራት ምንም ግዜ ሳይሰጥ እራስ ተኮር ትግል ያጧጡፋል:: ድሩን ያጠብቃል::

ትግሉን ሀ ብሎ ሲጀምር ከመሀሉ ያለውን ቅጥረኛ፣ ሎሌ፣ ሆድ አደር ባንዳ ባዳውን በማጥራት ስራውን ይጀምራል:: ውስጡን ሲያጠራ ከዱር ሆኖ ወጣቶችን የሚያሰለጥነው በፖለቲካም የሚቃኘው ሀይል በውድም በግድ ወደ ዱር አማራዊውን ያስገባል:: ወጣቱን ታዳጊ የአገር መሪ እና ጠባቂ ለማድረግ በፖለቲካ ያነቃል:: በአጭርና በረጅም ግዜ ያለውን አላማ በደንባድርጎ ያስጨብጣል::

አሁን ልጇ ዱር ያለ እናትም ሳትወድ በግድ ትነቃለች በአማራነቷልጇ ማንነቱን ሊያድን ሸፍቷልና:: ፀሎቷ ሁሉ “አማራን ነፃ አውጣልኝ” “ለጆቼ ድል ስጥልኝ” የሚል ይሆናል ማለት ነው:: ከሰማይም ከምድርም ሀይል ተቀናጀ ማለት ነው:: አባትም መሳሪያ ደብቆ ያስቀምጣል ይወለውላል ልጁ ሀይ ሲል ከዱር እሱ ከከተማ ሊያግዝ:: አ የትኛዋም አማራ እናት ማእከላዊው መንግስት ወርቅ ቢያፈስላት ልቧ ልጇ ያለበት ዱር ይቀራል:: ድጋፍ ተገኘ ማለት ነው:: እህትም ወድሟ ሲናፍቃት ዱር ትከተላለች:: ጓደኛዋ ሲዘምት ፍቅርም ያስገድዳል እንድትከተለው:: እሷም ብን ብላ ዱር:: ወንድሞችን ከመመገብ እስከ ጥበባዊ ምክር ብሎም በሰልፍ እስከማገዝ ትልቅ እገዛ ታደርጋለች ማለት ነው::

ከዛ አስተባባሪው ድምፅ ግፋ ሲል ጥቃት ከያቅጣጫው በመሰንዘር አማራዊ ምድርን ነፃ ለማውጣት በሽፍታ ስልት እያጠቁ ዋና ዋና ተቋማትና አውታሮች ላይ አደጋ በመጣል በመንግስት ወንበር ያለውን ወንበሩን ለማስለቀቅ አስገዳጅ ሆኖ ይታገላል:: እያለ ሁሉም አማራ ለአአንድ አማራ በሚል ይሰለፋል:: ትግሉም በድል ይጠናቀቃል:: አማራዊ አስተዳር አዋቅሮ አማራ ለአማራ በአማራ የሚለውን አሰራር በጊዮናዊ ሁሉን አቀፍነት የአማራ ብሄርተኝነት ባዲራውን ከፍ አድርጎ ይተክላል::

ትግል ብሎ ሰላም፣ ትግል ብሎ አዳራሽ የለም:: ታግሎ አሸንፎ ነው አዳራሽ የሚገባው!

ትግል ብሎ ዱር፣ ትግል ብሎ ማንቃት፣ ትግል ብሎ ብረት ነው ያለው::

ይቀጥላል…….